አፍሪካን በምስሎች፡ ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 2/2010

ታትሟል

ባሳለፍነው ሳምንት ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ከተሰባሰቡ ፎቶዎች መካከል የተመረጡ ምስሎች ስብስብ።

በሶማሊያ ዋና ከተማ የሞቃዲሾ ባህር ዳርቻ አቅራቢያ ልጆች በፈራረሱ ህንፃዎች መካከል ሲጫወቱና ሲዋኙ።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በኒውዚላንድና በደቡብ አፍሪካ ቡድኖች መካከል የተካሄደው የራግቢ ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት በባህላዊ አልባሳት ተውበው ሜዳው ላይ ዝግጅት ካቀረቡ ሰዎች መካከል።

በጋና ዋና ከተማ አክራ አደገኛ የእሳት ቃጠሎ እና ከባድ ፍንዳታ ያደረሰው ጉዳት በከፊል።

በግብፅና በኮንጎ ብራዛቪል መካከል አሌክሳንድሪያ በሚገኘው ቦርጅ ኤል አረብ ስታዲም ውስጥ የ2018 የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታን የታደሙ የግብፅ ደጋፊዎች።

ከሃያ ዓመታት በኋላ ግብፅ ኮንጎ ብራዛቪልን 2 ለ 1 አሸንፋ ለዓለም ዋንጫ ያለፈችበትን ጨዋታ በርካቶች ተከታትለውታል።

የቀድሞው ታዋቂ እግር ኳስ ተጫዋች የጆርጅ ዊሃ ደጋፊዎች ከምርጫው ቀን በኋላ የምርጫውን ውጤት ለማወቅ ሬዲዮ ሲያዳምጡ።

የኬንያ ተቃዋሚው ፓርቲ ናሳ ደጋፊዎች ናይሮቢ ውስጥ ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከአድማ በታኝ ፖሊሶች ጋር ተፋጠው።

ህግ አስከባሪዎች የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ደጋፊዎችንም በአይነ-ቁራኛ ይከታተሏቸዋል።

በግድግዳ ላይ ሥዕሎቹን በመስራት የሚታወቀው ፋልኮ የተባለው ሰዓሊ ደቡብ አፍሪካ ማዕከላዊ ጆሃንስበርግ ውስጥ የሳለው ግዙፍ የግድግዳ ላይ ሥዕል።

ፎቶዎች ከኤኤፍፒ፣ ኢፒኤ፣ ፒኤ እና ከሮይተርስ የተገኙናቸው።