ኮሮናቫይረስ፡ በኢኳዶር በኮሮና የሞቱ ሰዎች አስክሬን በየመንገዱ እየተጣለ ነው
ታትሟል
በኢኳዶር በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች አስክሬን በየመንገዱ እየተጣለ ነው።
በኢኳዶሯ ትልቋ ከተማ ጉዓያኪል ነዋሪዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ዘመዶቻቸውን ሳይቀብሩ ለቀናት መቆየት ግድ ሆኖባቸዋል።
የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ መንግሥት የሚሞቱ ሰዎችን አስክሬን ለመቅብር ከአቅሙ በላይ ሆኗል።
ባሳለፈው ሳምንት በኢኳዶር ጉዓያኪል ከተማ በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች አሰክሬን በየመንገዱ ተጥሎ የሚያሳይ ምስል የበርካቶችን ትኩረት ስቦ ነበር።