BBC News, አማርኛ - ዜና

ዜና

ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ

አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ

በአጭሩ ይመልከቱ ይዝለሉ ቀጥሉ

በአጭሩ ይመልከቱ

  • ፎቶ
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
  • ምሥል
  • የአቅራቢ እና የወታደር ምሥል
  • የመሪዎች ምሥል
  • ተማሪዎች
  • ፋሲካው
  • መንኮራኩር
  • የፊት ፎቶ
  • ፓይለት
  • አቅራቢ
  • የሚቃጠል መኪና

የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ

የሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ

  • የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

    የኢትዮ-ኤርትራ የዲፕሎማሲ ቁርሾ ባለፉት 36 ዓመታት

    ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እንደገና የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል። ይህ የቅርብ ጊዜ የዲፕሎማሲ ስብራት በሁለቱ አገራት መካከል ለአስርት ዓመታት የቆየውን ተለዋዋጭ ግንኙነት እንደገና ወደ ፊት አምጥቷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለፉት 36 ዓመታት ውስጥ ከቅርብ ወዳጅነት እና ትብብር እስከ ጦርነት፣ ከዚያም ወደ ረዥም የዲፕሎማሲ መራራቅና "ጦርነትም ሰላምም የሌለበት" ሁኔታ የደረሱ ሲሆን፣ በኋላም ዕርቅና የግንኙነት መሻሻል አሳይተዋል።

  • የትግራይ ሠራዊት አባል

    የአፋር ክልል የኤርትራ ወታደሮች ድንበር አልፈው በመግባት ውጊያ ከፍተዋል ሲል ከሰሰ

    የአፋር ክልል መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያ ድንበርን አልፈው በመግባት ከህወሓት ታጣቂዎች ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ሲል ለቢቢሲ ተናገረ። የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ መሃመድ አሊ ለቢቢሲ በክልሉ እየተዋጉ ነው ያሏቸው የኤርትራ ወታደሮች እንዲሁም ወታደራዊ ቁሳቁሶች መማረካቸውን ጨምረው አስታውቀዋል። የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ስለመግባቱ እና እየተደረገ ባለው ጦርነት ላይ በቀጥታ ስለመሳተፉ የፌደራል መንግሥቱ እስካሁን ድረስ ያለው ነገር የለም።

  • አዲስ አበባ ከተማ

    በአዲስ አበባ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ ፍንዳታ መሰማቱን ነዋሪዎች ተናገሩ

    በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ እና ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት ግለሰቦች ትናንት ሌሊት ከ6 ሰዓት በኋላ ከባድ ፍንዳታ መስማታቸውን ተናገሩ። ሮይተርስ የዜና ወኪል በበኩሉ የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ በአዲስ አበባ ረቡዕ እኩለ ሌሊት ፍንዳታ መሰማቱን ዘግቧል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው እና በጎተራ እና በቤተል አካባቢ የሚኖሩ ግለሰቦች ፍንዳታውን የሰሙት ከእኩለ ሌሊት 6፡20 በኋላ መሆኑን ተናግረዋል።

  • የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ አላማጣ ከተማ ሲገቡ የሚያሳይ ምስል

    በአላማጣ እና አካባቢው በነበረው ውጊያ ነዋሪዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት ምን እናውቃለን?

    በአላማጣ እና አካባቢው ደረሰ በተባለ የከባድ መሣሪያ ጥቃት ባለፉት ሦስት ቀናት ብቻ ቢያንስ ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪ እና አንድ የሆስፒታል ምንጭ ለቢቢሲ ተናገሩ። በአላማጣ ከመስከረም 16 እስከ 19፣ 2019 ዓ.ም. ድረስ ከባድ ውጊያ መካሄዱን እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አላማጣ ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

  • ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በኒው ዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ንግግር ሲያደርጉ

    ኢትዮጵያ "የውጭ ጣልቃ ገብነቶች ቢኖሩም ተቆጥባ እንደቆየች" ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ተናገሩ

    ኢትዮጵያ "የውጭ ጣልቃ ገብነቶች" ቢኖሩም እንኳን "በከፍተኛ ሁኔታ ተቆጥባ" እንደቆየች እና ከጎረቤት አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት "እንዳሻሻለች" ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ በኒው ዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስሯን በማጠናከር እና በሱዳን ሰላም እንዲሰፍን የሚደረጉ ጥረቶችን ብትደግፍም "የውጭ ኃይሎች ጣልቃ እየገቡ" እንደሆነ መግለጻቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

  • የኤምኤስኤፍ አርማ

    በጦርነቱ ተጎድተው በኮረም፣ አላማጣ እና ሽረ ሆስፒታሎች የታከሙ ሰዎች ቁጥር 720 እንደሚደርስ ኤምኤስኤፍ ገለጸ

    በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግመኛ ጦርነት በመቀስቀሱ ምክንያት ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 15፣ 2019 ዓ. ም. ድረስ በኮረም እና አላማጣ ሆስፒታሎች የገቡ ታካሚዎች ቁጥር በ48 ሰዓታት ውስጥ ከ180 ወደ 420 ከፍ ማለቱን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) አስታወቀ። ኤምኤስኤፍ መስከረም 18፣ 2019 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ በጦርነት ተጎድተው ወደ ሆስፒታል የሄዱ ታካሚዎችን ቁጥር ይፋ አድርጓል።

  • ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

    ኢትዮጵያ በአሥመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት መወሰኗን አስታወቀች

    ኢትዮጵያ በኤርትራ መዲና አሥመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት መወሰኗን እና 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ አገሪቷን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠቷን አስታወቀች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ሐሙስ መስከረም 21/2019 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ይህንን እርምጃ የወሰደው ኤርትራ "ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ" በሆነ መንገድ ለምትፈፅመው "የጠብ ጫሪነት እና የትንኮሳ" ድርጊቶች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ገልጿል። እርምጃውን ተከትሎ ኤርትራም ምላሽ ሰጥታለች።

  • ጠ/ሚ ዐቢይ እና ፕሬዝዳንት አል ሲሲ

    ግብፅ እና ኢትዮጵያ አንዳቸው የሌላኛቸውን ዲፕሎማት ለማስወጣት ወሰኑ

    ኢትዮጵያ የግብፅ ዲፕሎማት አሕመድ ሞሐራን አሕመድ ሶሊማን በ48 ሰዓታት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ ስትወስን ግብፅ በበኩሏ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን አስታውቃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዲፕሎማቱ ከአገር እንዲወጡ የተወሰነው "ዲፕሎማሲያዊ ጥሰት" በመፈጸማቸው መሆኑን አመልክቷል። ግብፅም በካይሮ ያሉት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በ48 ሰዓታት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ አሳስባለች።

  • ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

    የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ምን ተናገሩ?

    የህወሓት ሊቀ መንበር የሆኑት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች አዲስ ጦርነት መጀመሩን ተናግረዋል። የትግራይ ሕዝብ "የፖለቲካ ልዩነቶቹን ወደ ጎን ትቶ ለኅልውናው እንዲቆምም" አሳስበዋል። ደብረፅዮን ትናንት መስከረም 21/2019 ዓ. ም. በሰጡት መግለጫ፤ በውጊያው ያለውን ወታደራዊ ሁኔታ ሲያብራሩ የትግራይ ጦር "በተለያዩ አካባቢዎች እየተዋጋ መሆኑን" ገልጸዋል።

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

    ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉንም የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ማቋረጧን አስታወቀች

    ኢትዮጵያ በኤርትራ መዲና አሥመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት መወሰኗን እና 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከአገሪቱ እንዲለቁ ትዕዛዝ መስጠቷን ተከትሎ፤ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉንም የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ማቋረጧን አስታወቀች። ኢትዮጵያ ኤርትራን "በጠብ ጫሪነት እና የትንኮሳ" ድርጊቶች ስትከስ ኤርትራ በምላሹ፤ ኢትዮጵያ "እነዚህን ያልተገቡ የጠብ አጫሪነት ድርጊቶች ምክንያታዊ ለማድረግ ኤርትራን ከስሳለች" ብላለች።

  • ወታደሮች በመቀለ

    የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሸን ሊቀ መንበር የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠየቁ

    የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ውጥረት እና ወታደራዊ መካረር "እጅግ እንዳሳሰባቸው" ገለጹ። ግጭቱ "በአፋጣኝ እንዲቆምም" አሳስበዋል። ዛሬ ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ. ም. ማምሻውን ባወጡት መግለጫ፤ የመቀለ፣ የአክሱም እና ሽረ አውሮፕላን ማረፊያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው፣ ህወሓት የፌደራል መንግሥት ሠራተኞችን መያዙ እና የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎች መቋረጣቸው እንዳሰጋቸው አስታውቀዋል።

የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?

የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!

የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች

ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ

አነጋጋሪ ጉዳይ

ከየፈርጁ

አጃኢብ!

የተመለሱ ጥያቄዎች

ሌላ ዕይታ

በስፋት የተነበቡ