የኢትዮጵያዊያን የእግር ጉዞ በናይሮቢው የካሩራ ጫካ ውስጥ

ታትሟል

የኢትዮጵያዊያን የእግር ጉዞ በናይሮቢው የካሩራ ጫካ ውስጥ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስተዋወቂያ
የምስሉ መግለጫ, በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ናይሮቢ በሚገኘው የካሩራ ጫካ ውስጥ የእግር ጉዞ ተዘጋጅተው ነበር። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድጋፍ የተዘጋጀው የ5ኪ.ሜ እግር ጉዞ ቅድመ ዝግጅት።
የኢትዯጵያ ኤምባሲ በናይሮቢ አምባሳደር የሆኑት አቶ መለስ ዓለም
የምስሉ መግለጫ, በኬንያ የኢትዯጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ መለስ ዓለም የ5ኪ.ሜ እግር ጉዞን ለማስጀመር ባደረጉት ንግግር "ይህ ተግባር ተጠናክሮ በናይሮቢ ታላቁ የኢትዮጵያን ሩጫ የማናመጣበት ምንም ምክንያት የለም" ብለዋል።
የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ሮ መሰለች መኮነን
የምስሉ መግለጫ, የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ሮ መሰለች መኮንን የተሰባሰቡበትን ዓላማና ወደፊት ሊያደርጓቸው የሚችሉትን ዕቅዶች ለተሳታፊዎቹ በአጭሩ አካፍለዋል።
የካሩራ 5ኪ.ሜ እግር ጉዞ
የምስሉ መግለጫ, የእግር ጉዞው 'ድር ቢያብር አንበሳ ያስር' በሚል መሪ ሃሳብ ላይ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ዓላማውም በናይሮቢ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ግንኙነት ለማጠናከር ታስቦ ነው።
ተሳታፊዎች
የምስሉ መግለጫ, በተለያዩ የዕድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያ በእግር ጉዞው ላይ ተሳትፈዋል
የሚጨፍሩ ወጣቶች
የምስሉ መግለጫ, የእግር ጉዞው ተጀምሮ እስኪያልቅ በባህላዊ ዘፈንና ጭፈራ ዝግጅቱን ካደመቁት ተሳታፊዎች መካከል
የእግር ጉዞው ተሳታፊዎቹ
የምስሉ መግለጫ, የእግር ጉዞው ማጠናቀቂያ ላይ ተሳታፊዎቹ የተነሱት የቡድን ፎቶግራፍ