ዶ/ር ሰለሞን ክብረት፡ "ኮሮኖቫይረስን ለመከላከል ኢትዮጵያ ያላት አማራጭ አንድ ብቻ ነው"
ታትሟል
እንደሌሎች አገሮች ሁሉ የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያን በከፋ ሁኔታ የሚያጠቃበት እድል ቢፈጠር የመቋቋም አቅሟ ምን ያክል ነው? እንደእዚህ አይነት እንዳይፈጠር ወይም ከተፈጠረ በኋላስ መፍትሔው ምንድን ነው?
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የባዮሜዲካል ሳይንስ ተመራማሪ ሳይንቲስት የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ክብረት ኢትዯጵያ ቫይረሱን ለመከላከል ያላት አማራጭ አንድ ብቻ መሆኑን ይገልጻሉ።
ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በላይ ታማሚ ያላት አሜሪካ ከ2 መቶ ሺህ በላይ ቬንትሌተር ወይም የመተንፈሻ መሣሪያዎች አሏት። ኢትዮጵያ ግን ያላት የቬንትሌተር ብዛት ከ200 አይበልጥም ይላሉ። ይህም ማለት ለአንድ ሚሊዮን ሕዝብ ያለው ቬንትሌተር ሁለት ብቻ ነው።